አየር መንገዱ ያገኘው ፈቃድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ሞሪሸስ ለመብረር ጊዜያዊ ፈቃድ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡
አየር መንገዱ ከሞሪሸስ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባገኘው ፈቃድ መሠረት ከመጪው ሰኔ 8 እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ 30 በረራዎችን ለማድረግ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።
በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚኖረው በረራው ሞሪሸስን ከቀሪው የአኅጉሪቱ ክፍል ጋር በማገናኘት የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ እንዲሁም ወጪ እና ገቢ ንግድ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል፡፡
የሞሪሽስ የቱሪዝም ሚኒስትር ሪቻርድ ዱቫል ይህ አዲስ የአየር መስመር ግንኙነት ለሀገሪቱ ትልቅ ጥቅምን የሚወክል መሆኑንም መናገራቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
በዓለም ዙሪያ ከ125 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት እና በአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንኑ መዳረሻውን ለማስፋት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያረገ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹንም 26 አድርሷል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
