EthiopiaNews

የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በዘመን አይሽሬ እና በባሕላዊ ስራዎቿ የብዙዎችን ልብ የማረከችው አንጋፋዋ ድምፃዊትና የዜማ ደራሲ ራሔል ዮሐንስ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

በኪነ ጥበብ ህይወቷ በርካታ የማይረሱ ድንቅ ስራዎችን ለህዝብ በማበርከት ታላቅ ባለውለታ የነበረችው አርቲስቷ ስኬታማ የጥበብ ጉዞ እንደነበራት ሲነገር
ድምጻዊቷ ራሔል ዮሐንስ የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት ነበረች።

የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ምህረት ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል ቀን 8 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews