EthiopiaNews

የአይሮፕላን ግዥ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 67 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ ሊገዛ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

ከእነዚህ የቦይንግ ምርቶች ውስጥ 11 ፣ 787 ድሪም ላይነርስና በአስቸኳይ የሚገዙ ሌሎች 20ዎቹ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡
የአዳዲሶቹ አውሮፕላኖች ግዢ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በረራዎች ከፍ ለማድረግና በአዳዲስ የቦይንግ ኩባንያ ዘመናዊ ምርቶች ለማገዝ እንደሚያስችል ነው የቦይንግ ኩባንያ በመግለጫ ያመለከተው፡፡