የአይ ኤም ኤፍ እና የኢትዮጵያ ስምምነት
የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በተራዘመው የብድር አቅርቦት መርሃግብር አምስተኛው ግምገማ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በባለሙያዎች ደረጃ ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ።
አይ ኤም ኤፍ ባወጣው መግለጫ ስምምነቱ በገንዘብ ድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሲጸድቅ ኢትዮጵያ 468 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ገልጿል።
አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ በጠቅላላ የለቀቀው ብድር የአሁኑን ጨምሮ ወደ 2.65 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ነው የገንዘብ ድርጅቱ ያስታወቀው።
በወቅታዊው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ እና ማዳበሪያ ዋጋ ቢጨምርም፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጠንካራ ሆኖ መቀጠሉን የገንዘብ ድርጅቱ ገልጿል።
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት እና የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ እስካሁን መጠነኛ ነው ተብሏል። መረጃው ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
