በቀጣይ የሚካሄደው ልዩ ምርጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ድምጽ የሚሰጡበት ልዩ የምርጫ መርሃ ግብር እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ይሄንን ያስታወቁት በትላንትናው ዕለት በወቅታዊ የምርጫ ሂደት ላይ በሰጡት መግለጫ ነው።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባለፈው ሰኞ ተካሄዶ ቢጠናቀቅም ነገር ግን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመጪው ማክሰኞ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ እንደሚካሄድም ነው ሰብሳቢዋ የጠቀሱት፡፡
ተፈናቃዮች ባሉባቸው ቦታዎች እና በወታደራዊ ካምፕ የሚደረጉ ምርጫዎች በፍጥነት ተጠቃልለው መቅረብ የሚችሉ ውጤቶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።
በልዩ ሁኔታ በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ ወቅት ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እና 126 ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መመዝገባቸውን ቦርዱ መረጃ ያሳያል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews