የአ.አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለፉት 11 ወራት ከ38 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት ውስጥ ከ38 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል።
ጽህፈት ቤቱ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ42 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ አፈጻጸሙም የዕቅዱን 89 በመቶ ማሳካት የቻለ ሲሆን ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 ነጥብ 58 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ ከተጣራ ገቢ አንጻር 37 ነጥብ 44 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 33 ነጥብ 17 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ዓመት የ3 ነጥብ 82 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
