EthiopiaNews

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሚገኙ ለወባ በሽታ ወረርሽኝ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በሽታውን በዘላቂነት ለመቆጣጠር መንግሥትና ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በካፋ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች የተከሰተውን የወባ ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ ባከናወነው ስልታዊ ምርመራ የተለዩ ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ላይ ምክክር መደርጉን ጠቁሟል።

በአካባቢዎቹም የወባ በሽታን ለማከም እና ለመቆጣጠር አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት መኖሩ ተግዳሮት ሆኖ መቀጠሉ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን ስርጭቱን ለመቆጣጠር የታቆሩ ውሃዎችን ማፋሰስ፣ የኬሚካል ርጭት፣ የክትባት እና አጎበር ስርጭት እንዲሁም ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በመከናወናቸው በአሁኑ ወቅት በበሽታው የመያዝ ምጣኔ ሊቀንስ መቻሉን ገልጸዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv