የኢራን አዲስ የጦርነት ዕቅድ
የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሞሐሙድ ባገር የኢራን ጦርነት ዳግም ከተቀሰቀሰ ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር የምትጫወትበት አዲስ ወታደራዊ ካርድ በእጇ መኖሩን ገልጸዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ነገ የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ ሁለቱን ሀገራት ለማደራደር እየተደረገ ያለውም ጥረት ፍሬ እያፈራ አለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡
በፓኪስታን በዛሬው ዕለት ይደረጋል የተባለው የአሜሪካና የኢራን ሁለተኛ ዙር ድርድር ስለመካሄዱ ከሁለቱም ሀገራት በኩል እስካሁን የተሰጠ ማረጋገጫ ባይኖርም የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ወደ ፓኪስታን እንደተጓዙ የሀገራቸው መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው፡፡
በቴህራን በኩል የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከአሜሪካ ጋር የመደራደር ምንም ፍላጎት እንደሌላቸው እየገለጹ የሚገኙ ሲሆን ዋሽንግተን በኃይል የተቆጣጠረችውን የኢራን የጭነት መርከብ እንድትለቅም እየጠየቁ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው ስለመርከቧ ምንም ባይሉም የኢራን ወደቦች ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑት ቴህራን ከዋሽንግተን ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰች ብቻ ነው እያሉ ይገኛሉ፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
