EthiopiaNews

የኢራን የሰላም እቅድ

ኢራን ያቀረብኩት አዲሱ የሰላም ዕቅድ አሜሪካ በሁሉም የጦርነት ግንባሮች የተከፈተውን ጦርነት እንድታቆም፣ ለኢራን የጦርነት ካሳ እንድትከፍል እና ወታደሮቿን ለኢራን ቅርብ ከሆኑ አካባቢዎች ማውጣትን ያካትታል ማለቷ ተሰምቷል፡፡

የኢራን ምክትል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ እንደሚሉት ቴህራን አሜሪካ የጣለችባትን ማዕቀቦች እንድታነሳ፣ በምእራባዊያን ባንኮች እንዳይንቀሳቀስ የተጋደውን የኢራን ሀብት እንድትለቅ እና በሀገሪቱ ወደቦች ላይም ያስጣለችውን እግዳ እንድታነሳ ትሻለች፡፡

ሆኖም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን የቴህራንን ጥያቄዎች የማይረባ ሲሉ ማጣጣላቸው የሚታወቅ ቢሆንም በኢራን ላይ ከዛሬ ጀምሮ ሊፈጽሙ የነበረውን ጥቃት በጎረቤት ሀገራት ጥያቄ ለጊዜው ማቆማቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/