EthiopiaNews ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውጤት May 19, 2026 ebs news የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የግማሽ ቢሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ ዶላርን 159 ብር ከ98 ሳንቲም መሸጡን አስታወቀ።ባንኩ በዛሬው እለት ባደረገው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከተሳተፉት 30 ባንኮች ውስጥ 14ቱ አሸናፊ እንደነበሩ ገልጿል።በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታው የተሳተፉ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከፍተኛ ያቀረቡት ዋጋ 160 ብር ከ90 ሳንቲም የቀረበ ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 157 ብር ከ30 ሳንቲም ነበር ተብሏል።#EBS#EBSTVNEWS#EBSTVSPORT#_7696_WNhttps://t.me/ebstvnewshttps://ebstv.tv/