EthiopiaNews

ኢሰመጉ ያቀረበው ጥሪ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ኢሰመጉ መንግስት ሰዎችን አስገድዶ ከመሰወር ለመጠበቅ የወጣውን ዓለም አቀፍ ስምምነት በማጽደቅ የሀገሪቱ ህግ አካል እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ኢሰመጉ ይሄንን ጥሪ ያቀረበው በአማራ፣ አዲስ አበባና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የዜጎችን የመኖር፣ የአካል ደህንነት እና በነጻነት የመዘዋወር መብቶች ላይ ያነጣጠሩ አሳሳቢ ክስተቶችን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው፡፡

በአዲስ አበባ፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ላይ ከአንድ የፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት አቶ ተገኘ ባልቻ የተባሉ ግለሰብ መገደላቸውን የጠቀሰው የኢሰመጎ መግለጫ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝና ግልጽ ማጣራት በማካሄድ ከህግ አግባብ ውጪ የኃይል እርምጃ በወሰዱ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ጠይቋል፡፡

እንዲሁም የባህርዳር ከተማ ነዋሪና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ታደለ ጥበቡ የተባሉ ግለሰብ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ/ም በአማራ ክልል የፀጥታ አካላት መወሰዳቸውን የጠቀሰው ኢሰመጉ የክልሉ መንግስት ግለሰቡ የሚገኙበትን ሁኔታ በአስቸኳይ ይፋ እንዲያደርግ በመንግስት የፀጥታ አካላት ስር የሚገኙም ከሆነ ወደ ህግ እንዲያቀርባቸውም ነው የጠየቀው፡፡

የፌዴራል መንግስት እንዲሁም የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በተደጋጋሚ በታጣቂዎች በቤንሻጉል ጉሙዝ አካባቢ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በሕይወት የመኖር መብት፣ የአካል ደህንነት፣ የመንቀሳቀስ መብት ለማስከበር የሚያስችል አስተማማኝ የጸጥታ ጥበቃ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢፌድሪ ህገ መንግስት አስገድዶ መሰወርን በስብዕና ላይ የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን ቢገልጽም የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ላይ ይህንን አስገድዶ መሰወርን የሚቀጣ ድንጋጌ ባለመኖሩ የህግ ክፍተት እንደሚስተዋል በመግለጫው የጠቀሰው ኢሰመጉ መንግስት ይህንን ዓለም አቀፍ ስምምነት እንዲያጸድቅና የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ላይ በግልጽ የሚቀጣ ድንጋጌ እንዲያካትት ነው ጨምሮ ያሳሰበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/

Telegram (https://t.me/ebstvnews)
EBSTV NEWS
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox – @EbswhatsnewBot