InternationalNews

የኢራን የካሳ ጥያቄ

ኢራን ለአሜሪካ የጦር ሰፈር የሰጡ 5ቱ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በጦርነቱ ለደረሰባት ጉዳት ካሳ እንዲከፍሏት ጠየቀች።

ቴህራን ይሄን የካሳ ክፍያ ጥያቄ ያቀረበችው ለመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በፃፈችው ደብዳቤ ነው።

ቴህራን ካሳ እንዲከፍሏት የጠየቀቻቸው ለአሜሪካ የጦር ሰፈርን የሰጡ 5ቱ የአረብ ሀገራት ሳኡዲ አረቢያ ፣ አረብ ኢምሬትስ ፣ ኳታር ፣ባሕሬን እና ጆርዳን ናቸው።

ኢራን እነዚሁ 5ቱ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና እስራኤል በተፈፀመባት ጥቃት በቀጥታ ተሳታፊ እንደነበሩ ገልፃ በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳ ሊከፍሉኝ ይገባል ብላለች።

የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ኢራን ላደረሰችው ውድመት በአለም አቀፍ ደረጃ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል ሲሉ መጠየቃቸውን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/