EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ፓስፖርት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፋት 9 ወራት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት መስጠቱን አስታወቀ።

አገልግሎቱ ይሄን ያለው የ2018 ዓ/ም የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም በገመገመበት መድረክ ላይ ነው።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 824,951 ቪዛ መስጠቱን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በአየር እና በየብስ ድንበር ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ከ5.4 ሚሊየን በላይ ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ አስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ፣ በሕገ ወጥ ደላላዎችና የተቋሙን ስም በአሉታዊ መንገድ እንዲነሳ ያደረጉ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

መረጃው ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews