EthiopiaNews

አዲስ የአርኪዮሎጂ ግኝት

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በአፋር ስምጥ ሸለቆ በመካከለኛው አዋሽ የምርምር ፕሮጀክት ከ100 ሺህ ዓመታት በፊት ይኖሩ የነበሩ የጥንታዊ ሆሞ ሳፒየንስ ቅሪተ አካላት እና የድንጋይ መሣሪያዎች መገኘታቸውን አስታወቀ።

የመካከለኛው አዋሽ የአርኪዮሎጂ ጥናት ቡድን ያገኛቸውን አዳዲስና ትኩረት የሚስቡ ግኝቶች፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የአሜሪካ የሳይንስ ጆርናል “ፕሮሲዲንግስ ኦፍ ዘ ናሽናል አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ” ላይ ታትሞ ዛሬ መውጣቱ ተገልጿል።

የባለሥልጣኑ የአጥኚ ቡድን የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ጉዞንና ጥንታዊ የአኗኗር ዘይቤን የሚያሳዩ አዳዲስ የአርኪዮሎጂ ግኝቶችን ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ በዶ/ር ዮናስ በየነ የተመራና ከ24 አገራት የተውጣጡ ሳይንቲስቶች የተሳተፉበት የብዙ ዓመታት ምርምር ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

በጥናቱ የተገኘው መረጃ ኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ዳግም ያረጋገጠ ሲሆን፤ በአፍሪካ የሰው ዘር አመጣጥ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የመረጃ ክፍተት የነበረበትን ከ900,000 እስከ 200,000 ዓመታት ያለውን ጊዜ የሚዘክሩ አዳዲስ መረጃዎችን ይዟል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ዛሬ ይፋ የተደረገው የምርምር ውጤት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።

በምርምሩ የሆሞ ሳፒየንስ የሰው ዘር አመጣጥን፣ ሰዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩ የድንጋይ መሣሪያዎችን፣ የሰው ዘር ቅሪተ አካላትንና የተለያዩ የእንስሳት ቅሪቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

መረጃው ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews