EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የግንቦት ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.4 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አስታወቀ።

የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.6 በመቶ የጨመረ ሲሆን በዋናነት አትክልት፣ ስጋ ፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመራቸው የተመዘገበ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 11.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት (12.1 በመቶ)፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ (14.6 በመቶ)፣ ኮሙዩኒኬሽን (9.1 በመቶ) ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች (10.5 በመቶ) እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች (17.9 በመቶ) ሆነው ተመዝግበዋል። መረጃው ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv