EthiopiaNews

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀመረ።

ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ199 የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው 85,017 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸው ገልጾ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተናውን ሂደት የሚከታተሉ አመራሮችን ጨምሮ የጸጥታ አካላት እና የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውን አሳውቋል። መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv