የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል
በአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል በመጀመርያው ምድብ ከአዘጋጇ ሀገር ካሜሮን ጋር ተደልድሎ የነበረው ዋልያው ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 1 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ ከውድድሩ መሰናበቱ የሚታወስ ሲሆን በትላንትናው እለት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስም በፌዴሬሽኑ አባላትና በተለያዩ አካላት አቀባበል ተደርጎለታል። የኢትዮጵያ ከ 20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የፊታችን እሁድ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።በኮስታሪካ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ለማለፍ 2 የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ብቻ የሚቀራቸው እንስቶቹ በትላንትናው እለት በካፍ ልህቀት ማዕከል የሽኝት መርሃ ግብርም ተደርጎላቸዋል ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ወደ ስፍራው ማቅናቱም ተሰምቷል:: ምንጭ :- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwide
Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision