የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ታንዛንያ ዳሬ ሰላም የፊታችን ረቡዕ ይጓዛል፡፡ ሀምሌ 15 እና ሀምሌ 24 የደርሶ መልስ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያደርገው ዋልያው የመጀመሪያ ጨዋታውን ለመከወን ረቡዕ ረፋድ 4 ሰዓት ላይ 23 ተጫዋቾች እና ሌሎች የልዑካን ቡድን አባላትን በመያዝ ጉዞውን ወደ ታንዛንያ ዳሬ ሰላም የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ቡድኑ ዝግጅቱን በአዳማ ከተማ ሲጀምር መጠነኛ ጉዳት ገጥሞት የነበረው አማኑኤል ዩሃንስ ከህመሙ አገግሞ ልምምድ የጀመረ ሲሆን ሌሎች ተጫዋች ግን በሙሉ ጤንነት ላይ ተገኝተው ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ አርብ 10 ሰዓት ሲል በግዙፉ ቤንጃሚን ብካምባ የሚደረገው ጨዋታ ባለሜዳ በመሆን ደቡብ ሱዳን የመጀመሪያ ጨዋታዋን የምታደርግ ትሆናለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን የፊታችን አርብ ካደረገ በኋላ በዚያው በታንዛንያ ቆይታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ቡድኑ ሃምሌ 24 በዚያው በዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ብካምባ ላይ የመልስ ጨዋታውን በመከወኑ ምክንያትም ለተጨማሪ ቀናቶች ዝግጅቱን በታንዛንያ ላይ ያደርጋል፡፡
ሪፖርተር፡ ፈይሰል ዛኪር

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS