የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በ2014 አመት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተካሄደው እንቅስቃሴ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ተቋማዊ አቅምን መገንባት፣ የህግ ማቀፎችን መዘርጋትና ማሻሻል፣ረቂቅ ፓሊሲን ማዘጋጀትና የአሰራር ስረዓቶችን የመከለስና አለማቀፋዊ ማድረግን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን መስራቱን ያስታወቀው መስሪያ ቤቱ በ2014 የውድድር አመት ለ533 ስፖርተኞቾ ምርመራ ማድረጉንም ገልፅዋል፡፡

ከዚህ አኳያም የተወሰኑ የህግ መጣስ ሂደቶች እንደተፈፀሙ የገለፁት የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል 2 እግር ኳስ ተጫዋቾች እንዲሁም 1 አትሌት የህግ ጥሰቱን መፈፀማቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላው በውድድር አመቱ አለማቀፍ ግንኙነቶችን የማጠናከር ስራዎች መሰረታቸው በመግለጫው የተነገረ ሲሆን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች እንዲሁም ለሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱም ተያይዞ ተነስቷል፡፡

ለምርመራው የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስም የምርመራ ላብራቶሪ ሀገር ውስጥ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ መኮንን ይሄም ረዘም ያለ ጊዜን እንደሚወስድና የፍይናንስ አቅምን የሚፈትን መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር፡ ሳምራዊት ሃብቴ