Sports

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ያለበትን የደርሶ መልስ ጨዋታ አስመልክቶ እያደረገው ስለ ነበረው ዝግጅት የብሄራዊ ቡደኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የ2023 የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በአልጄሪያ መከወኑን ተከትሎ ዋልያዎቹ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሀምሌ 15 እንዲሁም ሀምሌ 21 የደርሶ መልስ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ታንዛንያ ዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ብካምባ ላይ የፊታችን አርብ በ10 ሰዓት ላይ ያደረጋሉ፡፡

ይህንን ተከትሎም ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሊጉ መጠናቀቅ መልስ ለተጫዋቾች እረፍት በመስጠት ሐምሌ 04 እና 05 ቅድመ ምርመራ በማድረግ ከሐምሌ 6 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ለጨዋታው ዝግጅት እንደጀመሩ አውስተዋል፡፡ በዚህም ከድካም ማገገሚያ እና ታክቲካል ስራዎች ላይ ያተኮረው መሰናዶ ለአምስት ቀናት በቀን አንዴ ቀሪውን አንድ ቀን ደግሞ ሁለት ጊዜ መደረጉን ደግሞ ጨምረው ተናግረዋል። ሰለተጋጣሚያቸው የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከሰኔ 28 ጀምሮ ወደ ዝግጅት ከመግባቱ በቀር ተጨማሪ መረጃ እንደሌላቸው ያነሱት አሰልጣኙ በዋልያዎቹ በኩል ግን ከ23 ተጫዋቾች መካከል አማኑኤል ዮሐንስ ፣ ዳዋ ሆቴሳ እና በዛብህ መለዮ ላይ ከነበረው መጠናኛ ጉዳት በቀር ስብስቡ ሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

አዳዲስ ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ በብዛት አለመካተታቸውን ተከትሎ ሃሳባቸውን ያነሱት አሰልጣኙ ቡድኑ መስከረም ላይ ለሚጠብቀው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ይህንን የማጣሪያ ውድድር እንደ መዘጋጃ ጭምር ስለሚጠቀም በነበረው ቡድን መቀጠልን እንደ ዋንኛ አማራጭ መጠቀማቸውን ገልፀዋል፡፡ ኮንትራታቸው ሊጠናቀቅ መቃረቡን ተመልክቶ ምላሻቸውን የሰጡት የዋልያዎቹ አለቃ ከፌዴሬሽኑ ጋር በውላቸው ዙሪያ ንግግር እያደረጉ እንደሚገኙ እና በሁለቱም አካላት መካከል ዳግም የመስራት ፍላጎት መኖሩን ጨምረው የገለፁ ሲሆን በቅርቡ በዚሁ ዙሪያ አዲስ ነገር ሊኖር እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ሪፖርተር፡ ፈይሰል ዛኪር

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS