የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተቀማጭ ገንዘቡን 92 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ማድረሱን ገለጸ ፡፡
ባንኩ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት በሀገሪቱ ፈር ቀዳጅ በመሆን የሼሪዓ ህግን መሰረት ያደረገ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በእምነታቸው ሳቢያ ከባንክ አገልግሎት የራቁ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ከዘርፉ ጋር ማቀራረብ መቻሉን አመልክቷል።
አገልግሎቱን በመስኮት ደረጃ ብቻ መስጠት የጀመረው ባንኩ አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ በ153 ቅርንጫፎች ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ብቻ እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህም 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ደንበኞችን በማፍራት 25 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለተጠቃሚዎች ፋይናንስ መደረጉን ጠቁሟል፡፡
የኢ ቢ ኤስ ዘገባ – ብሩክ አስቀናው