EthiopiaNews

የኢትዮጵያ እና ሳኡዲ አረቢያ ግንኙነት

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር ) የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ ጠየቁ።

ሚኒስትሩ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ከሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስትሩ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻችም ጠይቀዋል ተብሏል።

ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ህጋዊትን የተከተለ የስራ ስምሪት በሳኡዲ አረቢያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ደህንነትን መረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል።

መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/