EthiopiaInternationalNews

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በብራዚል

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት የሚረዳ የትብብር ስምምነት ትላንት በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚልያ መፈራረሙን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከአራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የወጣቶች ውይይት በኢትዮጵያ በመጪው አዲስ አመት ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

ይህን ዓለም አቀፍ የወጣቶች የምክክር መድረክ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በትብብር ለማዘጋጀት ከስምምነት ላይ የደረሱት ዓለም አቀፍ ተቋማት A common World Among the youth ፣ Abu Dhabi Forum for Peace (UAE) ፣ Network for Religious and Traditional Peacemakers እንዲሁም Stirling Foundation መሆናቸው ተናግርዋል፡፡

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በብራዚል ዋና ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 20 ሃገራት የዓለም አቀፍ የሃይማኖት መሪዎች የምክክር መድረክ ላይ እየተሳተፉ መሆኑ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለኢቢኤስ በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡