የኢጋድ ታዛቢ ቡድን
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ ) የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 2018 ዓ.ም ለሚደረገው የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢ ቡድኑ አዲስ አበባ መግባቱን አስታወቀ።
ታዛቢ ቡድኑ በቀድሞው የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ስፔሲኦዛ ዋንዲራ ካዚቢዌ የሚመራ መሆኑን ኢጋድ ገልጿል።
ታዛቢ ቡድኑ ከኢጋድ አባል ሀገራት የተውጣጡ የምርጫ ቦርድ ተቋማት ፣መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪክ ማህበራት እና የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት ያካተተ ነው ተብሏል።
የምርጫ ታዛቢ ቡድኑ 26 አባላት ያሉት መሆኑን ኢጋድ አሳውቋል።
ቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ግንቦት 26 2018 አ.ም በአዲስ አበባ በሚያካሂደው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ የመጨረሻ ሪፖርቱን ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቱን ይፋ ካደረገ በኋላ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
መረጃው ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ የተገኘ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
