የኤሌክትሪክ ቆጣሪ አዲስ አሰራር
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የገንዘብ ውስንነት ያለባቸው አዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ፈላጊ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ አሰራር ማስጀመሩን አስታውቋል።
በዚህ አዲስ አገልግሎት መሰረትም በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችሉ ዜጎች እስከ 2 አመታት የጊዜ ማራዘሚያ ተሰጥቷቸው አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ይህም መደበኛውን ወይም ነጠላ ፌዝ ቆጣሪ ለሚፈልጉ ደንበኞች ብቻ እንደሆነም ተነግሯል።
በሌላ በኩል አገልግሎቱ ባለፈው በጀት ዓመት ከግማሽ ሚሊየን በላይ አዳዲስ ቆጣሪዎችን የማገናኘት ስራ መሰራቱ የተገለጸ ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመትም ከ800 ሺህ በላይ አዳዲስ ቆጣሪዎችን ለማስገባት እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
