የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አደረገ፡፡

የእንግሊዝ መንግስት በአለም አቀፉ ጥምረት ኮቫክስ በኩል ለኢትዮጵያ ግማሽ ሚሊዮን ዶዝ አስራዜኒካ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የክትባቱን ድጋፍ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አሌክስ ካሜሮን በተገኙበት ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ርክክብ ተፈጽሟል፡፡

በርክክቡ ወቅት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አሌክስ ካሜሮን፤ የእንግሊዝ መንግስትና ህዝብ ለኢትዮጵያውያን ያለውን አጋርነትና ጥብቅ ወዳጅነት ለማጠናከር የታሰበ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የእንግሊዝ መንግስት ያደረገው ግማሽ ሚሊዮን የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወስደው ሁለተኛ ዙር ለሚጠብቁ ዜጎች እንደሚውል የተናገሩ ሲሆን በአዲስ አበባ ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ያሉ ሁሉም ዜጎችና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ዜጎች በሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማት በኩል ክትባቱን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሯ የእንግሊዝ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ማመስገናቸው ተነግሯል

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us