የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የክልሉ የ2019 ረቂቅ በጀት ከ704 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ለጨፌ እንዲመራ ወስኗል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የክልሉ የ2019 ዓ.ም ረቂቅ በጀት 704 ቢሊየን ብር ሆኖ ከተቀመጠ በኋላ ለማጽደቅ ወደ ክልሉ ከፍተኛ የሕግ አውጪ አካል ወደሆነው ጨፌ ኦሮሚያ እንዲመራ መወሰኑን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡
ይህ የበጀት ረቂቅ ካለፈው አመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የ303 ቢሊዮን ብር ጭማሬ ያለው ሲሆን የ2018 የክልሉ በጀት 400 ቢሊየን ብር ገደማ ነበር፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
