EthiopiaNews

ከሪል እስቴትና ከግለሰቦች በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው ስም ያላዞሩ ባለንብረቶች በፍጥነት ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ተጠየቁ

ከሪል እስቴት አልሚዎች እና ከግለሰቦች በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው ወደመሬት ተቋማት በመቅረብ ስም ያላዞሩና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ያልያዙ ባለንብረቶች ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ጥሪውን አስተላለፈ።

ቢሮው ቀደም ባለ ጊዜ በመሬት ላይ ያረፈን ንብረት ተሻሽጠው (ሸጠው/ገዝተው) እስካሁን የስመ-ንብረት ዝውውር ያላደረጉ (የይዞታ ማረጋገጫ) ያልያዙ አካላት በአጭር ጊዜ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል።

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ የስም ንብረት ዝውውሩ በወቅቱ አለመደረግ ንብረት ገዝተው ነገር ግን የንብረት ባለቤት ማረጋገጫ ያልያዙ ወገኖች ለጉዳት እየዳረገ ነው ብለዋል።

የቢሮ ኃላፊው ስለ ስም ንብረት ዝውውር ምንነት ሲናገሩም አንድ ሰው ያፈራውን ንብረት በራሱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን የሚያስተላልፍበት ስርዓት መሆኑን ጠቅሰው የመጨረሻው ግቡም የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫን መያዝ ነው ብለዋል።

ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ይሄንን ሳያደርጉ የቀሩ እና የሚቀሩ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ከዚህ በፊት ሽያጭ ተሻሽጠው ነገር ግን የስም ዝውውር / የይዞታ ካርታ በስማቸው ያላወጡ ባለንብረቶች ለአደጋ እንዳይጋለጡ በማሰብ መንግስት በአጠረ ጊዜ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ያቀርባል ብለዋል። መረጃው ከአዲስ አበባ ሚዲያ ኔትወርክ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv