የካፒታል ገበያ ማሳሰቢያ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባይራ አክሲዮን ማህበር የውሃ ፋብሪካ አቋቁማለሁ ወይም አርባምንጭ ውሃ በሚል በባለሥልጣኑ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለሽያጭ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
ባደረገው ክትትል ይሄንን ማረጋገጡን ያስታወቀው ባለሥልጣኑ ይህ እንቅስቃሴ የቅድመ-ማስታወቂያ ፈቃድ ሳያገኝ የተካሄደ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡
ማህበራዊ ሚድያን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያዎችን በመሰራጨት ላይ መሆኑን ደርሼበታሉ ያለው ባለስልጣኑ ይህ ተግባር በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑንም ገልጻል፡፡
አስተዳደራዊ ምርመራ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ባለሥልጣኑ ህብረተሰቡ አክስዮኖቹ በባለስልጣኑ ያልተመዘገቡና የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ለማሰራጨትም የባለስልጣኑን ይሁንታ ያላገኘ መሆኑን ተገንዝቦ ያልተመዘገቡ አክስዮኖችን ከመግዛት እንዲቆጠብ እንዲሁም ለማንኛውም የሽያጭ ወኪልም ሆነ ለአክስዮን ማህበሩ ክፍያ እንዳይፈጽም አሳስቧል።
ባለሥልጣኑ ባወጣው መግለጫ ጨምሮም የሚወስደውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቀሰ ሲሆን ሕዝቡም መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
