Ethiopia

የኮሚሽኑ የ10 ወራት ገቢ

ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት አስር ወራት ከ600 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ የበጀት አመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የእቅዱን 100 ነጥብ 2 በመቶ ማሳካቱን የገለጸ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ250 ቢሊየን ብር በላይ ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ሀገሪቱ በሕገወጦች የማጭበርበር ተግባር ልታጣ የነበረውን 228 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉ የተገለጸ ሲሆን በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ቁጥጥር በተሰሩ ሥራዎች ከ1 ሺህ 290 በላይ ግለሰቦችን ለሕግ ማቅረብ ተችሏል ነው የተባለው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv