Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በናይሮቢ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው አፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያን ተሞክሮ ማካፈላቸውን ገልጸዋል፡፡

በኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ የተገኙት ጠቅላይ
ሚኒስትሩ በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማትና የኃይል ሽግግርን በተመለከተ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ማካፈላቸውን ነው የገለጹት፡፡

በጉባኤው ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሀብቶች የተገኙ ሲሆን ከኬንያው ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤን ያዘጋጁት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በነገው ዕለት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv