የአየር መንገዱ ግዥ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6 ተጨማሪ ኤርባስ ኤ350 ሞዴል አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው።
ብሉምበርግ እንደሚለው አዲሶቹ የኤርባስ አውሮፕላኖች ሰፋ ያለ መጠን ወይም ዋይድ ቦዲ እንዲኖራቸው ሆነው የተፈበረኩ ናቸው።
አየር መንገዱ ከዚሁ የአውሮፓ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ 20 በመጠናቸው አነስ ያሉትን ኤርባስ ኤ220 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙ ነው የተገለፀው።
እነዚህ አነስተኛ አውሮፕላኖች ለቅርብ በረራ አገልግሎት እንዲሰጡ የታለሙ መሆናቸው ተመልክቷል።
አየር መንገዱ ለግዥው በመጀመሪያ ደረጃ ድርድር ላይ ያለ ሲሆን ግዥው ሲጠናቀቅ አውሮፕላኖቹ አየር መንገዱ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ተመራጭ አውሮፕላን እንዲሆን ያስችለዋል ይላል ከቢዝነስ ዘገባው ብሉምበርግ ያገኘነው መረጃ።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
