Ethiopia

የተቀጡ የአገልግሎቱ ሰራተኞች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የብልሹ አሰራርና የስነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ ከ1 ሺህ 130 በላይ ሰራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታወቀ።

እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰራተኞች መካከል 16ቱ ከስራ ሲሰናበቱ፣ 721 የሚሆኑት የደሞዝ ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 402ቱ ደግሞ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።

ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ ከ100 በላይ የሚሆኑት በደንበኞች ጥቆማ መሰረት የተከናወኑ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ተቋሙ በኦዲትና ክትትል አጣርቶ የደረሰባቸው መሆናቸው ተገልጿል።

አገልግሎቱ በተለይ በሙስና መጠቆሚያ መተግበሪያ አማካኝነት ከደንበኞች የደረሱትን ከ400 በላይ ጥቆማዎች መርምሮ በኃላፊዎችና በሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ጥቆማ የቀረበባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች የአዲስ ቆጣሪ ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥና አስቸኳይ ጥገና እንዲሁም የቢል አሰባሰብ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ተቋሙ ደንበኞች በዲጂታል አማራጮች ጥቆማ ማቅረባቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቦ ለጠቋሚዎች አስፈላጊውን ጥበቃና እውቅና እንደሚሰጥም ተናግሯል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv