የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ምህረት እንደተደረገላቸው አስታወቀ።
ለኢትዮጵያውያኑ ምህረት የተደረገው ሚኒስቴሩ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲና በጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤት በማስተባበር ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት መሆኑን ገልጿል፡፡
ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል ።
ሚኒስቴሩ ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተም ክትትል እያደረኩ ነው ብሏል።
ሚኒስቴሩ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከውጭ ሀገር ጉዞ ጋር በተገናኘ በማኅበራዊ ሚዲያና ሌሎች መንገዶች ከሚያሰራጯቸው ሀሰተኛ ማታለያዎች ሕብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡ መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
