የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ኢትዮጵያ ባለፉት 11 ወራት ከወጪ ንግድ ከ9.81 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን ተናገሩ።
ሚኒስትሩ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥ 8.48 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ከ9.81 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማስመዝገብ የዕቅዱን 115.66 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
ሚኒስትሩ ይህ አፈጻጸም ከባለፈው የ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው የ7.21 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ36.10 በመቶ ወይም የ2.6 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
