የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አደረገ።
አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ገልጿል።
አገልግሎቱ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ 20 እና የቅደመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 12 ይሰጣል ብሏል፡፡
የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከሐምሌ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሰጥ የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ፈተና ደግሞ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሰጣል ተብሏል፡፡
መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv