EthiopiaNews

የፈጠራ አውድ ርዕይ

11ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች የፈጠራ አውድ ርዕይ በዛሬው ዕለት በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአውደ ርዕዩ ዋና ዓላማ ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ወደ አደባባይ እንዲያወጡና የበለጠ በፈጠራ የተካነ አእምሮን እንዲገነቡ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እስከ ነገ ድረስ የሚካሄደው ይሀው አውደ ርዕይ ለከተማዋ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነም ተገልጿል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv