የዝንጀሮ ፈንጣጣ
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአፍሪካ መስፋፋቱን ተከትሎ በሽታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በቀጣዩ 6 ወራት የ135 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማስፈለጉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ገንዘቡ በአፍሪካ ወረርሽኙ በተከሰተባቸው ሀገራት አፋጣኝ የክትባት አቅርቦት ለማዳረስ ያለመ መሆኑን የተናገረው ድርጅቱ የሞንኪፖክስ ስርጭትን ለመግታት የሚረዳ የ6 ወር እቅድ ይፋ ማድረጉን ተናግሯል።
በዚህ ዓመት ወረርሽኙ በተሰራጨባቸው 12 የአፍሪካ ሃገራት ከ590 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ21 ሺ 300 በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸዉን መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል የዘገበው አፍሪካንኒውስ ነው።