EthiopiaNews

የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን እና  በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያን በይፋ መረቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ‘‘ዲጂታል ለልህቀት’’ በሚል ስያሜ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት ‎ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ ኩራት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ መሆኑን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ወሳኝ መሠረተ ልማት የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎችን ጊዜ ይቆጥባል፣ የሙስና ቀዳዳዎችን ይደፍናል፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ ያጎለብታል ሲሉም ገልጸዋል።

ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነውም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ስኬት እንድናጠናክር፣ ተሞክሯችንን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናካፍል፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንድንጓዝ በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡