EthiopiaNews

የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጠቅላላ ውጤት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ጠቅላላ ውጤት ይፋ የሚያደርግበትን መሰናዶ ማካሄድ ጀምሯል።

በመሰናዶው ላይ የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሄር ታዬ አፅቀ ስላሴ ፣  የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ተወካዮች እንዲሁም በርካታ የተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ታድመዋል።

በዚህ መሰናዶ መርሀግብር  መሰረት የጠቅላላ ምርጫ ውጤት  በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ነዋይ ይፋ እንደሚደረግ ያሳያል።

በመሰናዶው ላይ ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ያለፈባቸውን ሙሉ ሂደቶች የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን እንዲሁም የቦርዱን የበርካታ አመታት የስራ ሂደት የሚያሳይ ዲጂታል ማሳያም ለእይታ በቅቷል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀን አስቀድሞ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የፀደቁ የምርጫ ክልሎችን ይፋ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የነዚህ ውጤቶች ጥቅል ግኝት ይፋ እንደሚደረግ ነው የሚጠበቀው።

በዚህ በዛሬው መሰናዶ ይፋ የሚደረገው ለ501 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለ638 የከተማ አስተዳደርና ክልል ምክር ቤቶች የተወዳደሩ ፓርቲዎችና ግለሰብ እጩዎች ውጤት ይሆናል።

በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በ1139 የምርጫ ክልሎች ላይ የተወዳደሩት 42 የፓለቲካ ፓርቲዎች እንደሆኑ ይታወቃል። ዘገባው የሪፖርተራችን አቤል አበበ ነው።