EthiopiaNews

🗳️ የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሃይሉ ምን አሉ?

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በቅድመ ዝግጅት ቅሬታ አፈታት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሴት ተሳትፎ ላይ የህግና አሰራር ማሻሻያ አድርጓል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጫ የሴቶች ጥቃት መከላከያ የስራ መመሪያ አዘጋጅቷል።

ዲጂታል የእጩዎችና መራጮች ምዝገባ ስርአትን ከነ ውስንነቱ ተግብሮ ለዘመናዊነት የመጀመሪያ እርምጃ ተራምዷል።

ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በዲጂታል መራጭነት ተመዝግበዋል፤ ራሳቸውን መዝግበዋል።

10,438 የፓለቲካ ፓርቲና የግል እጩዎች የብቃት መስፈርት ማረጋገጥ ተችሏል።

ከ120 ሚሊዮን በላይ የድምፅ መስጫ ማሳተም ወደ ሀገር ማጓጓዝ ብሎም ወደ 52 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ ተችሏል።

በተጨማሪም ቦርዱ የክርክር መድረኮችን ለመጀመሪያ ግዜ ማዘጋጀቱና በመገናኛ ብዙሀን ማሰራጨቱ ሌላው የዘንድሮ ምርጫ ስኬት ተደርጎ ተጠቅሷል።

በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ምርጫ አስፈፃሚዎችን ማሰልጠን ማሰማራትና መቆጣጠርም ሌላው ፈታኝ ሂደት ነበር ብለዋል።

በልማት አጋሮች ሲሰሩ የነበሩ የምርጫ ስራዎች በቦርዱ ሰራተኞች ሙሉ አቅም የተሰሩበት የምርጫ ወቅትሜ እንደነበር አንስተዋል።

በሎጂስቲክ አቅርቦትና በፀጥታ ችግር የተነሳ ምርጫው በግዜው አይካሄድም ተብሎ ተሰግቶ ነበር ያሉት ሰብሳቢዋ ፓለቲካዊ ጫናን በማስወገድና በገለልተኝነት በመመራት ስራችንን አከናውነናል ብለዋል።

በመራጮች ምዝገባና ምርጫ ቀን የክትትል ቡድን በማሰማራት የህግ ጥሰት ጣልቃ ገብነት ለመከላከል ተሰርቷል።

የአካባቢ አስተዳደር ጣልቃ ገብነትና መሰል ችግሮችን በመንቀስ በድምፅ መስጫ ቀን ጭምር ጥሰት የፈፀሙ  አስፈፃሚዎችን እንዲሰናበቱ ተደርገዋል።

ይህ ሁሉ ስራ የተሰራው በቦርዱ ብቻ ሳይሆን ወኪሎቻቸውን በማሰማራት በአግባቡ በተሳተፉ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና በሚዲያ ተቋማት  የጋራ ጥረት ነው ያሉት ሰብሳቢዋ የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ታዛቢዎችንም ለምርጫው ስኬት አመስግነዋል።

በድምፅ መስጫ ቀን ቀንና ሌሊት ሳይሉ ድምፃቸውን የሰጡ ዜጎች፣ የምርጫ ታዛቢዎች፣ የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም የቦርዱ ሰራተኞችና የምርጫ አስፈፃሚዎች ለዚህ ስኬት ሊመሰገኑ የሚገባቸው ናቸው ብለዋል ዋና ሰብሳቢዋ።

ከአስፈፃሚዎች መካከል የምርጫ ሂደትን ለማስፈፀም ሲጓዝ በደረሰበት አደጋ ህይወቱ ያለፈው የእነሞር ኢነር ምርጫ ክልል ሀላፊ  ዳዊት ዳንኤልም ስሙ ተዘክሯል።