EthiopiaNews

🗳️ የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያዎች ሴቶች ማህበር  ዳይሬክተር ስለምርጫው ምን አሉ? 🗳️

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫም ታዛቢ ነበርኩ ያሉት ዳይሬክተሯ ህብረት አባሆይ በሴቶች ላይ የሚስተዋሉ ጥሰቶችን ለማስወገድ የቴክኒክ ቡድን በማቋቋም የምርጫ ሂደቱ ለሴቶች ጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆን መስራት ተችሏል ብለዋል።

ይሄንን ለመከታተል የሚያስችል ቅፅ ተዘጋጅቶ ሲሰራ ነበርም ነው ያሉት።

ቦርዱ ተጎጂን ያማከለ ስርአት በመዘርጋት ያደረገው ጥረት ሴቶች ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማገዙን አንስተዋል።

10 አባላት የያዘ ብሄራዊ ግብረ ሀይል በማሰናዳት ለሴቶች ጥቃት ሁሉን አቀፍ ምላሽ ተሰጥቷል።

የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል ለፀጥታ አካላት፣ ለሚዲያዎችና ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ሁሉ ተገቢ ስልጠና ተሰጥቷል።

ማህበሩ ከ2 አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ለራሱ ታዛቢዎች አሰልጥኖ በ9 ክልል በሚገኙ 18 ዞን በ136 ምርጫ ጣቢያ ምርጫውን መታዘቡንና የመጀመሪያ ደረጀ ሪፓርትም ማውጣቱን ጠቅሰዋል።

ምርጫውን በታዘበባቸው ቦታዎች 97.8 በመቶ ሰላማዊ ነበር የሚል ውጤት ይፋ አድርጓል።

92.5 በመቶ ነብሰ ጡሮች፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች በድምፅ መስጫ ቀን ቅድሚያ አግኝተዋል። ሂደቱም ግልፅ ነበር።

በቅድመ ምርጫው 42 የጥቃት አይነት መመዝገቡንም አግስተዋል።

በምርጫው እለት በጥሪ ማእከል 8 ሴቶች የጥቃት ቅሬታዎች አቅርበዋል።

በተጨማሪም ከፓሊስ የቀረበ 1 ትምራን ከተሰኘ ጥምረት ደግሞ 11 የጥቃት ሪፖርት ቀርቦ በማጣራት ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

ግኝቱ ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ ቢሆንም ስራው አላለቀም ነው ያለው ማህበሩ።

ጥቃቶቹ እየተመረመሩ ናቸው ይህን የተመለከተ ሪፖርት ወደፊት የሚያወጣ ይሆናልም ነው ያሉት።

24.3 በመቶ ሴቶች ምርጫ ጣቢያ እንዲመሩ ማድረግ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አክሎም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተተገበረው  ተጎጂዎችን ያማከለ የምርጫ ጥቃት መከላከልና ምላሽ ስርአት እንዲጠናከር አክሎም ጥሪ አቅርቧል።