የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ማህበረሰቡ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀረበ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይሄን ጥሪ ያቀረበው የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ለሀገራዊ አንድነትና መረጋጋት፣ ለዜጎች ደህንነት እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፈተና መደቀኑን አስመልክቶ ባመጣው መግለጫ ላይ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመግለጫው ዜጎች የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በመቃወም እንዲያጋልጡ ጥሪውን አስተላልፏል።
መረጃው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
