የውጭ ምንዛሬ ክምችት
ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከዕዳቸው አንጻር ያለው ድርሻ በአውሮፓውያኑ በ2010 ከነበረበት 44 በመቶ በ2024 ወደ 28 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገልጿል።
ይህ የተገለጸው ኢትዮጵያ የዕዳ ጫናን ለመፍታት ያለመውን ሁለተኛውን የአፍሪካ የሉዓላዊ ሀብት አስተዳደር መድረክን በዛሬው ዕለት ባስጀመረችበት ወቅት ሲሆን በመድረኩም በአሁኑ ወቅት 8 የአፍሪካ አገራት በዕዳ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙና 14ቱ ደግሞ ከፍተኛ የዕዳ ስጋት እንዳለባቸው እንዲሁም የአህጉሪቱ አጠቃላይ የውጭ ዕዳ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱም ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን ጫና ለመቀነስ የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያና የአገር ውስጥ ገቢን የማሳደግ እንዲሁም በገበያ የሚመራ የውጭ ምንዛሬ ተመንን ጨምሮ የተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እያደረገች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በመድረኩ ገልጸዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
