InternationalNews

የአሜሪካ ውሳኔ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው በሆርሙዝ ሰርጥ መውጫ ያጡ መርከቦችን አጅባ ለማስወጣት የጀመረችውን ኦፕሬሽን ማቆሟን አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባጋሩት መልዕክት ሀገራቸው ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር ፍሬ ያፈራ እንደሆነ ለማየት ሲባል ለተወሰነ ጊዜ ኦፕሬሽኑ መቆሙን ጠቁመዋል፡፡

የኢራን ባለስልጣናት ስለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የጀመሩት ኦፕሬሽን መክሸፉን ላለመግለጽ ሲሉ በድርድር አሳበዋል ያሉ ሲሆን ቴህራን በዚህ ግጭትም ድል አድራጊ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሀገራቸው በኢራን ላይ የምትፈጽመው መልሶ ማጥቃት መቋጨቱን እና አሜሪካም በኢራን ጦርነት ማሳካት የፈለገቻቸውን ዓላማዎች ማሳካቷን መጠቆማቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv