InternationalNews

የፕሬዝዳንቱ የግል ሹመት

የማሊ መከላከያ ሚኒስትር መገደላቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሳሚ ጎይታ እራሳቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸው ተነገረ።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሳዶ ካማራ ታጣቂዎች በመላ ሀገሪቱ ላይ በከፈቱት የተቀናጀ ጥቃት ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገደላቸው የተሰማው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡

ይህንንም ተከትሎ በመፈንቅለ መንግስት ላለፉት 4 ዓመታት የሀገሪቱ መሪ የሆኑት አሳሚ ጎይታ እራሳቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አድርገው የሰየሙ ሲሆን የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ጄኔራል ኦማር ዲያራ ረዳታቸው ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሁለቱን የሀገሪቱ ስልጣን ለመቆጣጠር የተገደዱት መንበራቸው በመነቅነቁ ስልጣናቸውን ለማጠናከርና ስር ለማስያዝ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews