InternationalNews

የአሜሪካ ቪዛ እገዳ

በአሜሪካ ከሚኖሩ የቻይና ሕገ ወጥ ስደተኞች ጋር በተያያዘ አሜሪካ በቻይና ዜጐች ላይ የቪዛ እገዳ ለመጣል እየተዘጋጀች መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የተሰማው ደግሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ10 ቀናት በኋላ ቻይናን ይጎበኛሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ ላይ መሆኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ንግግር ጥላ እንዳያጠላበት ተሰግቷል ተብሏል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ህገ ወጥ ስደተኞቻቸውን ለመቀበል ዝግጁ ባልሆኑ ሀገራት ላይ ማዕቀብና ታሪፍ ለመጣል ደጋግሞ ቢዝትም ቻይና ዜጎቿን አረጋግጣ እንደምትወስድና ይህም ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ደጋግማ መግለጿ አይዘነጋም፡፡

በአሜሪካ ከ100 ሺህ በላይ ሰነድ አልባ ቻይናዊያን እንደሚኖሩ ሲነገር ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑት አሜሪካን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የተፈረደባቸው እንዲሁም 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ደግሞ እስር ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews