የፕሬዝዳንት ታደሠ ወረደ ውሳኔ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ታደሠ ወረደ የሕወሃት ቡድን ከሰሜኑ ጦርነት በፊት የነበረውን የክልሉን ምክር ቤት ወደነበረበት ለመመለስ የወሠነው ውሳኔ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ውድቅ የሚያደርግ ነው አሉ፡፡
የትግራይ የቀድሞው ምክር ቤት ወደ ቦታው መመለሱ ምን አሉታዊና አወንታዊ ውጤቶች እንደሚኖሩት መገንዘብ እንደሚያስፈልግ በሰጡት መግለጫ የጠቀሱት ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሥራውን እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የአስተዳደሩ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
በቅርቡ ለተጨማሪ አንድ አመት የአስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይሁንታ ያገኙት ታደሰ ወረደ ይሄንን የተናገሩት ሕወሓት ከጦርነቱ በፊት ምርጫ ቦርድ ውድቅ ባደረገው ክልላዊ ምርጫ የተመረጠው የክልሉ ምክር ቤት ወደ ሥራው እንዲመለስ መወሠኑን ተከትሎ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
