EthiopiaNews

የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ምዝገባ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የዘመን ባንክ አክስዮን ማህበር የሰነደ ሙአለ ንዋይ የምዝገባ መግለጫ ማጽደቁን አስታውቋል።

በሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዘመን ባንክ አክስዮን ማህበርን የምዝገባ መግለጫ ማጽደቁን ያስታወቀው ባለስልጣኑ በዚህም መሰረት በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው ያሉ አስራ አምስት ሚሊዮን አክስዮኖችን መመዝገቡን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ ይህንን ያሳወቀው ሰነደ ሙአለ ንዋይ ለመሸጥ ወይም እንዲሸጡ ለማድረግ ሳይሆን ሰነደ ሙአለ ንዋዮች በባለስልጣኑ መመዝገባቸውን ለሕዝብ ለማሳወቅ ብቻ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ባለስልጣኑ ጨምሮም በሰነደ ሙአለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ መሰረት ከምዝገባ ነጻ ከተደረጉ ውጪ ያሉ ለህዝብ የሚቀርቡ ወይም የሚሸጡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መመዝገብ ያለባቸው መሆኑን በመግለጽ መመሪያው ከመውጣቱ በፊት በህዝብ የተያዙ ሰነደ ሙአለ ንዋዮችም መመዝገብ ያለባቸው መሆኑን አሳስቧል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews