EthiopiaNews

የመሶብ የሞባይል አገልግሎት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሶብ የሞባይል አገልግሎትን በይፋ ማስጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሀገራዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ የሆነ የባህል ለውጥ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል።

‎መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጀመርነው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም፣ በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል ያሉ ሲሆን ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያመላከተ ነው ብለዋል።

ዛሬ በይፋ የተመረቀው የመሶብ የሞባይል አገልግሎትም የዚሁ ቀጣይነት ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አካል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፣ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን የምንቀጥል ይሆናል ነው ያሉት።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews